በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የዜጎች መብቶች
ይህ መብት የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 38(1)(ሀ) ስር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ያለምንም ልዩነት ‹በቀጥታና በነጻነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በህዝብ ጉዳይ አስተዳደር የመሳተፍ› መብት አለው በማለት በደገገው መብት ውስጥ የሚታቀፍ ነው፡፡
በሌላ አነጋገር ህዝቡ በመረጣቸው እንደራሴዎች አማካኝነት እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት መብት ነው ይህ መብት፡፡
ስለዚህ ዜጎች ምርጫ በአንድ ወይ በሌላ መልኩ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው በነቂስ ወጥተው ድምጽ መስጠት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛና ተዓማኒ ምርጫ እንዲካሄድ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡