በአማራ ክልል ገቢን በመሰብሰብ የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ገቢን በተገቢው መንገድ በመሰብሰብ የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ።
የቢሮው ሃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) እንዳሉት ÷ ክልሉ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የሕዝቡን የመልማት ፍላጎት ለማርካት በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው።
በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት ከተለያዩ ዘርፎች 100 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውሰዋል፡፡
እስካሁን ድረስም 50 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 50 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡
በኤሌክትሮኒክስ ታክስ አስተዳደር ሥርዓት ግብር ከፋዮች ባሉበት ሆነው ክፍያ መፈጸም እንዲችሉ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊው አመልክተዋል፡፡
በቀሪ ወራት ለመሰብሰብ የታቀደውን ገቢ ለማሳካትም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በሰላም አሰፋ