Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የማዕድን ሃብት ልማት ሥራን ይበልጥ ለማጠናከር…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የማዕድን ሃብት ልማት የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪ ወጪን እየቀነሰ ነው አለ የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ኃይሌ አበበ እንዳሉት÷ በክልሉ ማዕድን የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋነኛ ምሰሶ ተደርጎ ከተወሰደ ወዲህ ዘርፉን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበርና ሳይንሳዊ ምርምር በማካሄድ ከውጭ የሚገቡ ውድ የማዕድን ውጤቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሥራ መጠናከሩን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከዚህ በፊት በዘርፉ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችና ጥርጣሬዎች ሙሉ በሙሉ ተቀይረዋል ነው ያሉት ሃላፊው፡፡

በአሁኑ ወቅት ክልሉ እያመረታቸው ያሉ የማዕድን ውጤቶች የውጭ ምንዛሪ ወጪን ለመቀነስ ትልቅ አቅም እየሆኑ መምጣታቸውን አስረድተዋል።

በተለይም ከዚህ ቀደም ከቻይና እና ቱርክ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ይገቡ የነበሩት እንደ ግራናይት፣ ማርበልና የድንጋይ ከሰል ያሉ ምርቶች በክልሉ እየተመረቱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ዘርፉን ዘመኑን በዋጀ መንገድ በሳይንሳዊ ምርምርና በእውቀት ለመምራት ከወልድያ፣ ደብረ ማርቆስ እና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ባህላዊ የኦፓል እና የድንጋይ ከሰል አምራቾች በዘመናዊ መዋቅር ተደራጅተው ወደ ሕጋዊ ምርት መግባታቸውን ጠቅሰዋል።

በሶስና አለማየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.