Fana: At a Speed of Life!

ለብዝሀ ኢኮኖሚ ልማት የተሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ልማት እያከናወነቻቸው ያሉ የልማት ስራዎች የሚታይ ውጤት እያስገኙ ነው አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፡፡

የምስራቅ አፍሪካን የንግድና ኢንቨስትመንት አቅም ወደ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር የሚያስችሉ እድሎች ላይ ያተኮረው ኢሊቬት አፍሪካ 2026 በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትግበራ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እየሰራች ትገኛለች፡፡

በማሻሻያ ሂደቱ የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ መቀመሯን ገልጸው፥ በብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ልማት እያከናወነቻቸው ያሉ የልማት ስራዎች የሚታይ ውጤት እያስገኙ ነው ብለዋል፡፡

ኢሊቬት አፍሪካ ከጉባኤ የተሻገረ የገበያ ማዕከል መሆኑን በመረዳት ኢትዮጵያ እድሉን ለመጠቀም ዝግጁ መሆኗን አመልክተዋል፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፥ በዕውቀትና ክህሎት ሀገርን ውጤታማ ማድረግ ዘመኑ የሚጠይቀው አርበኝነት መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቱን ኃይል በማብቃት በዘርፉ ያለውን አቅም ለመጠቀም የሚያስችሉ ስራዎች እየተተገበሩ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

በጉባኤው ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች፣ አልሚዎችና ስራ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.