Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ፕሮግራም የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ጠቃሚ ነው – ዶ/ር መቅደስ ዳባ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ፕሮግራም የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ጠቃሚ ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፡፡

4ኛው ዙር የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት የእውቅና መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በወቅቱ እንዳሉት፤ ጥምረቱ ከምስረታው ጀምሮ የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ፍላጎትና የሆስፒታሎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እየሰራ ይገኛል።

በዚህም በሆስፒታሎች መካከል ጠንካራ ትስስር በመፍጠር የህብረተሰቡን የህክምና የአገልግሎት ፍላጎት እርካታ ለማሳደግ ምቹ አሰራር እንደፈጠረ ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሕክምና ቁሳቁስ የማሟላት ስራ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው፤ እንደ ሀገር 64 የኦክስጂን ማምረቻ ተቋማትን ማቋቋም መቻሉን አስረድተዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በበኩላቸው አዳዲስ አሰራሮች እና ፈጠራዎችን በመጠቀም ሆስፒታሎች አገልግሎቶቻቸውን ማሻሻል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በ4ኛው ዙር የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት የእውቅና መርሐ ግብር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 30 ሆስፒታሎች ተሸልመዋል።

በሔብሮን ዋልታው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.