Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ውስጥ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በቡርቃ ቀበሌ ውስጥ የተሰራው የገጠር ኮሪደር ከአካባቢው በተገኘ ቁሳቁስ መገንባቱን አስረድተዋል፡፡

የገጠር ኮሪደር ሥራው በሕብረተሰብ ተሳትፎ የተሰራ የአነስተኛ መንደር ሞዴል ክንውን መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ እቅድ እና ተግባራዊ የአሰራር ውጤትን ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.