በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰጡ ሹመቶች…
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚሽነርና ምክትል ኮሚሽነር ሹመቶችን ሰጡ፡፡
በዚህም መሰረት ሌ/ጄኔራል አስራት ደኔሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡
እንዲሁም ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እና አቶ ኤርዚቅ ኢሳ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሮች በመሆን መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።