Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጋሞ ዞን ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ሐዘናቸውን ለመግለጽ አርባምንጭ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ተመልሰው በቀጥታ ወደ አርባምንጭ አቅንተዋል።

በቆይታቸውም በአርባ ምንጭ ዙሪያ እና በመላው ጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሐዘናቸውን በመግለጽ የሚከናወኑ የድጋፍ ሥራዎችን እንደሚገመግሙ ተመላክቷል፡

‎የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት÷ ለቀናት የዘለቀው ከባድ ዝናብን ተከትሎ በአካባቢው የተከሰተው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የዜጎቻችንን ሕይወት ቀጥፏል፤ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል ሲል ገልጿል።

ከመጠን በላይ የሞላው የኩልፎ ወንዝም መንደሮችን፣ ቤቶችን፣ የእርሻ ስፍራዎችን፣ የአካባቢ መሠረተ ልማትን አውድሟልም ነው ያለው።

ማሕበረሰቡ በከባድ ሀዘን በሚገኝበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የነፍስ አድን ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ከተጎጂ ቤተሰቦች ጎን መቆም እንደሚገባ አስገንዝቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.