ምርጫ ቦርድ 30 በመቶ የሚሆነውን የመንግስት የመጀመሪያ ድጋፍ ለፓርቲዎች ለቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 30 በመቶ የሚሆነውን የመንግስት የመጀመሪያ ድጋፍ ለፓርቲዎች ለቅቄያለሁ አለ።
ቦርዱ ለተመዘገቡ እጩዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የእጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል።
የቦርዱ የህግ አማካሪ አይተነው ደበበ የእጩዎችና የፓርቲዎችን ስም፣ ምልክት እና ምስል በድምፅ የሚወሰንበት ሥርዓት መደንገግ የምርጫ ሂደቱ ግልፅ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሆነ ተናግረዋል።
የድምፅ መስጫ ወረቀት የእጩዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስም መለያ ምልክትና የእጩዎችን ምስል በመያዝ ታትሞ የተዘጋጀና መራጮች ለሚፈልጉት እጩ ድምፅ የሚሰጡበት ወረቀት መሆኑንም ገልጸዋል።
በመድረኩ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉን ጨምሮ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን÷ ምርጫ ቦርድ እስካሁን የሰራቸውን ስራዎች አቅርቧል፡፡
በዘርዓያዕቆብ ያዕቆብ