የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ በዓሉን አስመልክቶ ያዘጋጀው ዐውደ ርዕይ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ በዓሉን አስመልክቶ ያዘጋጀው ዐውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከፍቷል።
ዐውደ ርዕይውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር እና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ከኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እና ከሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆንነው መርቀው የከፈቱት።
ዐውደ ርዕይው ተቋሙ ከምስረታ ጀምሮ የነበረውን ጉዞ እና ሀገራዊ ለውጡን መነሻ አድርጎ በተቋማዊ ሪፎርሙ ያስመዘገባቸውን ስኬት የሚያስቃኝ መሆኑ ተመላክቷል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ በዓሉን “በአዲስ ምዕራፍ ለተሻለ ነገ” በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እያከበረ ይገኛል።
በዓድዋ ድል መታሰቢያ ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው ዐውደ ርዕይው÷ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።