ከ28 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ28 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።
ከየካቲት 28 ቀን ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በዲጅታል እና በማኑዋል አማራጭ እየተከናወነ ይገኛል።
የመራጮች ምዝገባ ሂደትን አስመልክቶ ቦርዱ ባወጣው መረጃ፤ የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ እስካሁን ድረስ 28 ሚሊየን 366 ሺህ 310 መራጮች ተመዝግበዋል።
ለመራጭነት ከተመዘገቡት ዜጎች ውስጥ 13 ሚሊየን 47 ሺህ 743 ሴቶች ሲሆኑ፤ 15 ሚሊየን 317 ሺህ 57 ደግሞ ወንዶች ናቸው።