Fana: At a Speed of Life!

በለውጡ ዓመታት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተሰሩ ሥራዎች ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር የብዙ ቤተሰብ ሕይወትን እየቀየረ ይገኛል፡፡

ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተደማሪ አቅም የሆነው የሌማት ትሩፋት ለዘመናት ጸጋ ሆነው ያልታዩ ጓሮዎችን የልማት ከባቢ ያደረገ ነው፡፡

የመደመር እሳቤ ያፈለቀው የፈጠራ ተግባር የእንስሳት ተዋጽኦን በአግባቡ ወደ ሌማት እንዲመጣ ማድረግ ችሏል፡፡

የሌማት ትሩፋት ከከበረው የሰዎች ሕይወትና ጤና፣ ከትልቁ የሀገር መልክና ክብር እንዲሁም ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ርዕይ ጋር የተሳሰረ ነው፡፡

ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

በሀገሪቱ ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በተለያዩ ዘርፎች በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችም ተመዝግበዋል፡፡

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በምግብ ራስን ለመቻል ከተጀመረው ትልቅ ተግባር በተጨማሪ ለበርካታ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማህበረስብ ክፍሎች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

በዚህም መርሐ ግብሩ የወተት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የዶሮና እንቁላል ምርትን በመጨመር፣ የማር እና የሥጋ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከምርት እስከ ገበያ እንዲሁም ገበታ ድረስ ያለውን የእሴት ሰንሰለት በማጠናከር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በወንድማገኝ ፀጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.