የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸውን የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎችን ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሠረት ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች በተፈጥሮ ሳይንስ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ፊዝክስ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።
ፈተናው በየትምህርት ዓይነቱ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል።
የዝግጅት አግባቡም 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት ላይ ያተኩራል።
ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡