ኢራንና አሜሪካ ተመትቶ የወደቀውን ተዋጊ ጄት አብራሪ ባልደረባ ለማግኘት እየተሽቀዳደሙ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢራንና አሜሪካ በኢራን ጦር ተመትቶ የወደቀውን ኤፍ -15 ተዋጊ ጄት አብራሪ ባልደረባ ለማግኘት እሽቅድድም ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ኤፍ-15 የተሰኘው የአሜሪካ ተዋጊ ጄት በትናንትናው ዕለት በኢራን አብዮታዊ ዘብ በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ተመትቶ መውደቁ ይታወሳል፡፡
የአሜሪካ ጦር የተዋጊ ጄቱ አብራሪ መገኘቱንና አብሮት የነበረው ባልደረባ ግን እስካሁን ያለበት አለመታወቁን አስታውቋል፡፡
ይህን ተከትሎም የጠፋውን የተዋጊ ጄቱ አብራሪ ባልደረባ ለማግኘት የአሜሪካ ሃይሎች የሚያከናውነት ፍለጋ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡
የኢራን ሃይሎች በበኩላቸው÷ የተዋጊ ጄቱን አብራሪ ባልደረባ ለማግኘት በአካባቢው ከፍተኛ ፍለጋ እያደረጉ እንደሚገኙ ተጠቅሷል፡፡
የኢራን ባለሥልጣናት ተዋጊ ጄቱ ተመትቶ በወደቀበት አካባቢ የሚገኙ ዜጎች ግለሰቡን እንዲፈልጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የተዋጊ ጄቱን አብራሪ ባልደረባ በሕይወት ይዞ ለሚያመጣ ማንኛውም ዜጋ የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጠው ይፋ ማድረጋቸውንም የሀገሪቱን መገናኛ ብዙሃን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በመላኩ ገድፍ