Fana: At a Speed of Life!

የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቡሩንዲ ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ዛሬ የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለናቸዋል ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ያኖሩ ሲሆን÷ ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ፋና ወጊ የሆነውን የዓድዋ ድል ታሪክም አስጎብኝተናቸዋልም ነው ያሉት።

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለነበረዎት ቆይታ እያመሰገንኩ፤ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካውያን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የሚኖርዎት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.