Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ የክሩዝ እና ፀረ የጦር መርከብ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰሜን ኮሪያ ሁለት ስትራቴጂክ ክሩዝ ሚሳኤል እና ሶስት ፀረ የጦር መርከብ ሚሳኤል ሙከራ በተሳካ ሁኔታ አድርጋለች፡፡

የሚሳኤል ሙከራዎቹ ቾኢ ሂዮን ከተባለው የሰሜን ኮሪያ አውዳሚ የጦር መርከብ ባለፈው እሁድ የተካሄዱ መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡

የሙከራው ዋና ዓላማ የጦር መርከቧን  የተቀናጀ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር እና የአሰሳ ሥርዓት ለመፈተሽ እንዲሁም ለመርከቧ የአሰሳ አባላት ሚሳኤሎቹን መተኮስ ማለማመድ ነው ተብሏል፡፡

በሙከራው ክሩዝ ሚሳኤሎቹ ከ7 ሺህ 800 በላይ ሴኮንድ እንዲሁም ፀረ የጦር መርከብ ሚሳኤሎቹ ከ1 ሺህ 900 ሴኮንድ በላይ አየር ላይ መቆታቸው ተገልጿል፡፡

የሚሳኤል ሙከራውን የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከከፍተኛ ወታደራዊ እና የባህር ኃይል መኮንኖች ጋር በመሆን  ተከታትለውታል ነው የተባለው፡፡

በዚህ ወቅት ኪም ጆንግ ኡን÷ የሀገሪቱን የኑክሌር ፕሮግራም ማጠናከር ቅደሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

የሀገሪቱ ጦር ኃይል የማጥቃት እና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅሙን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነ መግለጻቸውንም ቲ አር ቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.