የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ክፍተቶችን ለማረም በትኩረት ይሰራል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ክፍተቶችን ለማረም በትኩረት ይሰራል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፡፡
የኦሮሚያ ክልል የ2018 ሦስተኛ ሩብ ዓመት የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቅቋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ እንዳሉት÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል፡፡
በመድረኩ የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
በቀሩት ወራቶች 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ሽመልስ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም የ2019 በጀት ዓመት እቅድን ነባራዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ለማዘጋጀት ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡