Fana: At a Speed of Life!

መዲናዋ ባሏት የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ የስፖርታዊ ክንውኖች ትኩረት ማዕከል ሆናለች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቅርብ ዓመታት በተገነቡ የስፖርት መሰረተ ልማቶች አዲስ አበባ ከተማ ዓለም አቀፍ የስፖርታዊ ክንውኖች ትኩረት ማዕከል መሆን ችላለች አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ተገንብቶ የተጠናቀቀውን (የ46 ሜዳ) የስፖርት ሜዳ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
የ46 ሜዳ በርካታ የስፖርት ዓይነቶች የሚካሄድበት ዘመናዊ እና ሁሉንም ያሟላ የወጣቶች ማዘውተሪያ እንዲሆን ተደርጎ መገንባቱን ገልጸዋል።
የእግር ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ቮሊቦልና እጅ ኳስ፣ የተመልካቾች መቀመጫ፣ ሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚሰራባቸው ያሟላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለተጫዋቾች አገልግሎት የሚሰጡ ሻወር እና ሽንት ቤት አካቶ መያዙም ተጠቁሟል።
በውስን ቦታዎች ብቻ የነበሩት የስፖርት ማዘውተሪያዎች በየአካባቢው በማስፋት በቅርበት ወጣቶች ስፖርታዊ ክንዉኖች የሚያደርጉባቸው እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ከንቲባዋ በመልዕክታቸው።
በአካል ጠንካራ፣ በብቃት ተወዳዳሪ የሆኑ ወጣቶችን ለማፍራትና ለዘርፉ ዕድገት የስፖርት መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ እንደሆነ ገልጸዋል።
መዲናዋ በቅርብ ዓመታት በተገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ምክንያት ዓለም አቀፍ የስፖርታዊ ክንውኖች ትኩረት ማዕከል መሆን ችላለች ነው ያሉት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.