ከ46 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ46 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል አለ።
ከየካቲት 28 ቀን ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በዲጅታል እና በማኑዋል አማራጭ እየተከናወነ ይገኛል።
የመራጮች ምዝገባ ሂደትን አስመልክቶ ቦርዱ ባወጣው መረጃ፤ የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ እስካሁን ድረስ 46 ሚሊየን 732 ሺህ 895 መራጮች ተመዝግበዋል።
ለመራጭነት ከተመዘገቡት ዜጎች ውስጥ 21 ሚሊየን 515 ሺህ 693 ሴቶች ሲሆኑ፤ 25 ሚሊየን 217 ሺህ 202 ደግሞ ወንዶች ናቸው።
ከተመዘገቡት ውስጥ 69 ሺህ 286 ሴቶች እና 96 ሺህ 441 ወንዶች አካል ጉዳተኞች መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል።