Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ በሚያዚያ ወር ብቻ ለ4ኛ ጊዜ ያስወነጨፈችው ባላስቲክ ሚሳኤል…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰሜን ኮሪያ በዛሬው ዕለት በርካታ የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ምስራቅ ባሕር አስወንጭፋለች፡፡

ፕዮንግያንግ ዛሬ ያደረገችው የሚሳኤል ሙከራ ከፈረንጆቹ 2026 ወዲህ ለ7ኛ ጊዜ ሲሆን ÷ በሚያዚያ ወር ደግሞ አራተኛዋ ነው፡፡

በሀገሪቱ ሲንፎ በተሰኘ አካባቢ የተወነጨፉት ባላስቲክ የአጭር ርቀት ሚሳኤሎች 140 ኪሎ ሜትር ወይም 87 ማይል ርቀት መምዘግዘጋቸው ተመላክቷል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ጦር በበኩሉ ሰሜን ኮሪያ በየጊዜው የምታስወነጭፋቸውን ባላስቲክ ሚሳኤሎች በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ፕዮንግያንግ ለምትፈጽመው የትኛውም ትንኮሳ አስፈላጊውን አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ጦሩ አመልክቷል፡፡

የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ያስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች ምንም አይነት ጉዳት ሳያደርሱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዞን አቅራቢያ ወድቀዋል ማለቱን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.