Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ 6 ዘመናዊ ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስድስት ዘመናዊ ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።

አየር መንገዱ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ከኩባንያው ጋር ያደረገው ግዙፍ ስምምነት የአየር ላይ የበላይነቱን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

የአውሮፕላኖቹ ግዢ ከአዲስ አበባ ወደ አውሮፓ፣ እስያና ሰሜን አሜሪካ የሚደረጉ አህጉር አቋራጭ በረራዎችን ይበልጥ ምቹና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

አውሮፕላኖቹ በነዳጅ ቆጣቢነታቸው እና በጭነት አገልግሎት ውጤታማነታቸው ተመራጭ እንደሆኑም ተገልጿል።

ይህ ግዢ አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ያለውን ግዙፍ የድሪምላይነር ስብስብ ይበልጥ የሚያጠናክርለት ይሆናል ተብሏል።

አየር መንገዱ እንዲህ ያሉ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች ውስጥ መግባቱ በ2035 በዓለም ቀዳሚ ከሆኑ 20 አየር መንገዶች ተርታ ለመሰለፍ የያዘውን ግብ እንደሚያፋጥነው ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.