Fana: At a Speed of Life!

የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ 3ኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ 3ኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።

በ3ኛ ዙር ድጋፉም 500 ሺህ ሰርጂካል ማስክ፣ 65 ሺህ ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ፣ 10 ሺህ የህክምና ባለሙያዎች አልባሳት እና የጫማ መሸፈኛ ይገኙበታል።

እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰርጂካል ጓንቶች እና የአይን መሸፈኛ ጎግል መነፀሮችም በድጋፉ እንደተካተቱ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ አስታውቋል።

የቻይና መንግስት የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ከዚህ ቀደም በመጋቢት እና ሚያዝያ ወር ላይ በሁለት ዙሮች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

ከዚህ በተጨማሪም ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ላይ ከቻይና የተላኩ የህክምና ባለሙያዎች ቡድን አባላት በኢትዮጵያ ለ15 ቀናት ቆይታም አድርገው ነበር።

ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የህክምና ባለሙያዎቹ ቆይታቸውም ልምዳቸውን ያጋሩ ሲሆን፥ በተጨማሪም ምክሮችን ለጤና ባለሙያዎች እና ለህክምና ተቋማት ማካፈላቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.