ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት ተቀበሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል።
የመሪዎቹ ግንኙነት ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር በኢትዮጵያ የሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አካል ነው።
የመሪዎቹ ውይይት በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና የወል የትብብር መስኮችን በማጠናከር ላይ ያተኩራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቅላይ ሚኒሰትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡