Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካርጎ ላንድ ኤክሰለንስ ሽልማት የሁለት ዘርፍ ተሸላሚ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ላንድ ኤክሰለንስ ሽልማት ላይ በሁለት ዘርፎች ተሸላሚ ሆኗል።

አየር መንገዱ በቤልጂየም ሊዥ ከተማ በተካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ የካርጎ ዊንግስ ተሸላሚ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም አየር መንገዱ በምርጥ አጋርነት ዘርፍም ልዩ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

ሽልማቱ ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት እና በሊዥ አየር ማረፊያ ከሚገኘው ካርጎ ላንድ ጋር የገነባውን ጠንካራ አጋርነት ማሳያዎች እንደሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጀርመን ሀምቡርግ ከተማ በተካሄደው የ2026 የፓክስ ሪደርሺፕ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ የ3 ዘርፎች ሽልማቶች ባለቤት መሆኑ ይታወሳል።

በመርሐ ግብሩ በአፍሪካ ደረጃ “ምርጥ የምግብ አገልግሎት” እና “ምርጥ አጠቃላይ የመንገደኞች ተሞክሮ” እንዲሁም “ለሕፃናት የሚቀርብ ምርጥ የአገልግሎት ቁሳቁስ” በተሰኙ ዘርፎች ነው ያሸነፈው።

ይህም ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን መሪነት ከማጠናከር ባሻገር አየር መንገዱ በ”ራዕይ 2035″ ስትራቴጂው ከዓለም ቀዳሚ የአቪዬሽን ግሩፖች ተርታ ለመሰለፍ የያዘውን ግብ ይበልጥ የሚያሳልጡ መሆናቸውን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.