Fana: At a Speed of Life!

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አወያዮች መረጣ በመጠናቀቅ ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የአወያይነት ሚና የሚጫወቱ ግለሰቦች መረጣ እየተጠናቀቀ ነው አለ።
ኮሚሽኑ የተለያዩ መስፈርቶችን በመጠቀም የአወያዮቹን ምርጫ ሲያካሂድ ቆይቷል።
መስፈርቱንም አሟልተው ለተለዩ አወያዮች ከሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል።
ስልጠናው አወያዮች በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ወቅት የሚኖሩ ውይይቶች የምክክር ዓውድን ባገናዘበ፣ በብቃት፣ በታማኝነት እና በገለልተኝነት እንዲመሩ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.