Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፋብሪካዎችን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ፋብሪካዎችን በዛሬው እለት መርቀው ከፍተዋል፡፡
ፋብሪካዎቹ የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ሁለተኛው ምዕራፍ፣ ኦርጅን እና ሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎች እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሶላር መሠረተ ልማቶቹ በጋራ በዓመት 11 ነጥብ 3 ጊጋዋት ንጹህ ኃይል የሚያመነጩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40 ሺህ ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ያቀርባል ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የብዙዎችን ኑሮ መደገፍ ችለዋል ነው ያሉት።
‎ከፍተኛ የማምረት ዐቅም ያላቸው ፋብሪካዎቹ የኢትዮጵያን እምቅ ሐብት ወደ ጥቅም የቀየሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.