Fana: At a Speed of Life!

የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ የብሔራዊ ቤተ መንግሥት ሙዚዬምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ የብሔራዊ ቤተ መንግሥት ሙዚዬምን ጎብኝተዋል፡

ጉብኝቱ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አካል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

የጉብኝት መርሐ ግሩ የኢትዮጵያን ነፃና ጥንታዊ ሥልጣኔ የሚያሳይ ሲሆን÷ የሀገሪቱ ታሪክና ቅርሶችም ለታማኝና ባለርዕይ አጋርነቷ ህያው ምስክሮች ሆነዋል።

ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት መሆኗን የሚያሳዩ ታሪካዊ ቅርሶቿን ስታጋራ፣ ጥንታዊ ጥንካሬዋ ለዘመናዊውና ለውጥን ለሚያረጋግጠው አጋርነቷ መሠረት መሆኑን በድጋሚ እያረጋገጠች፤ አፍሪካውያን ወንድሞቻችንን ለጋራ የወደፊት ዕጣ-ፈንታ በአንድነት ለመሥራት ወደ ሁለተኛ ቤታቸው እንዲመጡ ጥሪ የምታቀርብበት ነው።

#PMOEthiopia

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.