Fana: At a Speed of Life!

ለተሻገረ ገጠርና ግብርና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የማይተካ ሚና አለው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለተሻገረ ገጠር እና ግብርና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የማይተካ ሚና አለው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘውን ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም በእርሻው በ250 ሄክታር ላይ 27 ዓይነት የቋሚ ተክል የሰብልና በፍጥነት ደራሽ የፍራፍሬ ልማት በተቀናጀ መልኩ እየተመረተ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የግብርና ሥራ እንዲስፋፋ ለሚደረገው ሥራ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል።

ይህ በግል ባለሀብት እየለማ ያለው የግብርና ሥራ እንደ ሶላር ያሉ የኃይል አማራጮችን እና የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም በመስኖ በማልማት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የግብርና ልማት እና የገጠር ሽግግር ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት።

ከተክል እና የሰብል ልማቱ ጎን ለጎንም የማር ምርት ላይ የሠጠው ትኩረት የአካባቢ እምቅ ፀጋ የመጠቀም ዕይታችን በግሉ ዘርፍ እየሠረፀ መሆኑን ተመልክተንበታል ሲሉ ገልጸዋል።

በእርሻው የዶሮ እርባታ፣ የንብ ማነብና የእንስሳት ልማት የተጀመረ ሲሆን÷ የመኖ ዝግጅት መጀመሩም ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በለይኩን አለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.