ፕሬዚዳንት ትራምፕን ያላስደሰተው በኢራን በኩል የቀረበ የድርድር ነጥብ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለት ወራት የዘለቀውን ጦርነት ለመቋጨት ኢራን በቅርቡ ባቀረበችው የመደራደሪያ ነጥብ ደስተኛ አይደለሁም አሉ።
ኢራን በቅርቡ ያቀረበችው የመደራደሪያ ነጥብ ጦርነቱ እስኪቆም ድረስ የኒውክሌር ድርድርን ወደ ጎን የተወ እንደሆነ ሮይተርስ የኢራን ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
በዚሁም ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር መርሐ ግብር ስምምነት እንዲዘገይ በሚጠይቀው የድርድር ነጥብ ላይ ደስተኛ አለመሆናቸውን ነው የአሜሪካ ባለሥልጣናት የገለጹት።
የኢራን የመደራደሪያ ነጥብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የመርከቦችን እንቅስቃሴ እልባት የሚሰጥ ቢሆንም÷ በአሜሪካ በኩል የኒውክሌር መርሐ ግብር ጉዳይ ወደ ጎን የሚተው ሳይሆን ቀይ መስመር ተደርጎ ተወስዷል።
ይህም የኃይል አቅርቦት ያስተጓጎለውን፣ የነዳጅ ዋጋ ያናረውን እና የሺዎችን ሕይወት የቀጠፈውን ጦርነት ለማስቆም የነበረውን ተስፋ የሚያጨልም ተደርጎ ተወስዷል።
በብርሃኑ አበራ