ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአሶሳ ከተማ የተገነባውን የግራናይት ፋብሪካ ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የተገነባውን የግራናይት ፋብሪካ ጎብኝተዋል።
ፋብሪካው እንደ ሀገር ለማዕድን ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ግንባታው ተጠናቅቆ ከወራት በፊት ወደ ስራ መግባቱ ተመላክቷል።
በክልሉ ያለውን የማዕድን ሃብት ወደ ጥቅም ለመቀየር እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተጨማሪ የሃብት ምንጭ ለመፍጠር የጎላ ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እንዲሁም ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልሉ ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በለይኩን ዓለም