የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ከ117 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ117 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ፡፡
የድርጅቱ የበጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) እንዳሉት÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የድርጅቱ የኦፕሬሽን አገልግሎት መጠን 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ቶን ደርሷል።
የስምሪትና ቁጥጥር ሥራዎች በቴክኖሎጂ መታገዝ፣ ሀገር አቋራጭ የመርከብ ንግድ ሥራዎች መስፋፋትና ወጪን የቀነሰ አሰራር መከተል ለውጤት ማብቃቱን ጠቅሰዋል፡፡
የድርጅቱ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዋና ክፍል ኃላፊ ስንታየሁ ኃ/ማሪያም በበኩላቸው ÷ የገቢ መጠን ማሳደግ፣ የመርከቦችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን የመጫን አቅም በመጨመር ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን ማጎልበት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በትኩረት የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
በግዛቸው ግርማዬ