Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለኢንቨስትመንት የሚውሉ ሃብቶችን ለማልማት የባለሃብቱ ሚና…

በአማራ ክልል ለኢንቨስትመንት የሚውሉ ሀብቶችን ለማልማት የባለሀብቱ ሚና…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአ‎‎ማራ ክልል ለኢንቨስትመንት የሚውሉ ሃብቶችን ለይቶ በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማጎልበት እየተደረገ ባለው ጥረት ባለሃብቱ ሚናውን ሊያጠናክር ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ።

በባሕር ዳር ከተማ መሬት ወስደው በኢንቨስትመንት ዘርፍ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

አቶ አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ‎ክልሉ በግብርና፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች የዕምቅ ሃብቶች ባለቤት በመሆኑ በማልማት ክልሉንና ሀገሪቱን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ባለሃብቱ ሚናውን ሊያጠናክር ይገባል።

በተለይም በግብርና ዘርፍ ክልሉ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶች በብዛትና በጥራት የሚመረትበት በመሆኑ ባለሃብቶች በዘርፉ ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

በማዕድን ዘርፍ የኦፓል፣ የወርቅ፣ የብረት፣ የድንጋይ ከሰልና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ ሃብቶች በመኖራቸው አልምቶ ለመጠቀም ባለሃብቶች በዘርፉ የበለጠ ሊሳተፉ ይገባል ብለዋል።

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ምርት የተሸጋገሩና በግንባታ ላይ የሚገኙ ባለሃብቶች ሥራቸውን በማጠናከር የክልሉን ልማት እንዲያፋጥኑ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የክልሉ መንግሥት በዘርፉ የሚስተውሉ የብድር፣ የኤሌክትሪክ አግልግሎትና የመንገድ መሠረተ ልማት አቅርቦት ክፍተቶችን ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.