Fana: At a Speed of Life!

ኢራን ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ለመግባት የሞከሩ የአሜሪካ የጦር መርከቦችን በሚሳኤል መምታቷ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢራን ያስተላለፈችውን ማስጠንቀቂያ በመተላለፍ ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ለመግባት የሞከሩ የአሜሪካ የጦር መርከቦችን በሚሳኤል መምታቷ ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ ባህር ኃይል በሰርጡ መተላለፊያ አጥተው የቆሙ መርከቦችን አጅቦ ለማስወጣት ዘመቻ እንደሚጀምር ገልጸው ነበር፡፡

ለዚህ ዘመቻ 15ሺህ ወታደሮች፣ ከምድርና ከባህር የሚነሱ ከ100 በላይ የጦር አውሮፕላኖች እንዲሁም የጦር መርከቦችና ድሮኖች ዝግጁ መሆናቸውን የአሜሪካ ጦር አስታውቋል፡፡

የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ የአሜሪካ ባህር ኃይል ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ለመግባት የሚሞክር ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠንቅቋል፡፡

ይህንን የቴህራን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት በሰርጡ ለማለፍ በሞከሩ የአሜሪካ የጦር መርከቦች ላይ ሁለት የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን የኢራን መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ የጦር መርከቦቹ ወደ ሰርጡ ያደርጉት የነበረው ጉዞ መገታቱ የተገለጸ ሲሆን፥ የአሜሪካ ጦር በበኩሉ በጦር መርከቦቻችን ላይ የተፈጸመ ጥቃት የለም በማለት አስተባብሏል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.