Fana: At a Speed of Life!

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባዔውን መጀመር አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ሁሉም ወገኖች ችግሮችን በሰላም ብቻ ለመፍታት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ከሰላም ውጪ የሚወሰድ የትኛውም አማራጭ ለዘላቂ ሰላም እንደማይበጅ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሕዝቡን ወደ አንድነት፣ ፍቅር፣ ሰላም እና ወደ ፈሪሃ እግዚአብሔር ማምጣት የጉባዔው አላማ መሆኑን አውስተዋል፡፡

በጉባዔው ላይ የቤተክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ሁኔታዎች፣ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች እንዲሁም ሀገራዊ ሰላምን የተመለከቱ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በየዓመቱ በግንቦት ወር የሚካሄደው የርክበ ካህናት ጉባዔ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድነትና ጥንካሬ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተመልክቷል፡፡

በአልማዝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.