Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥታዊ ተልዕኮዎችን እየተወጣ ነው – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥታዊ ተልዕኮዎችን እየተወጣ ነው አሉ፡፡
“በሕገ መንግሥት ትርጉም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣን፣ የዳኝነትና የፍትሕ ተቋማት ሚና” በሚል ርዕስ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በመድረኩ እንዳሉት፤ የግልና የቡድን መብት በማስከበር በርካታ ስራዎች በምክር ቤቱ ተሰርተዋል።
በተጨማሪም ሕገ መንግሥት የአንድ ሀገር የበላይ ህግ ብቻ ሳይሆን ህዝቦች በጋራ ለመኖር የተስማሙበት ቃል ኪዳን እና የመንግሥት ስልጣን ገደብ የሚቀመጥበት ሰነድ ነው ብለዋል።
በመሆኑ የሕግ የበላይነትን እና የመንግሥት ስልጣን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ባለ ድርሻ አካላት በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል።
በዙፋን አምባቸው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.