Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በሐረር ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነባቸውን ቤቶች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሐረር ከተማ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት አስረክቧል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ ትኩረት ከተሰጣቸው ሰው ተኮር ሥራዎች መካከል የዜጎችን ሕይወት ማሻሻል በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

በተለይም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሕዝብን ክብር የሚመጥኑ ተግባራትን እውን ለማድረግ የሚከናወኑ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ላከናወናቸው እና እያከናወናቸው ለሚገኙ ሰው ተኮር ተግባራት ምስጋና አቅርበዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ሚኒስቴሩ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉ ከሚከውናቸው ሥራዎች ባለፈ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም በ28 ሚሊየን ብር ወጪ በሐረር ከተማ የተገነቡና የቤት ቁሳቁስ ያሟሉ 12 ቤቶች ለተጠቃሚዎች መተላለፋቸውን ገልጸዋል።

በተስፋዬ ሃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.