ሩሲያ 81ኛ ዓመት የድል በዓሏን በሞስኮ ቀዩ አደባባይ እያከበረች ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ በ2ኛው የዓለም ጦርነት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችውን ድል 81ኛ ዓመት መታሰቢያ በተለያዩ ስነስርዓቶች እያከበረች ነው፡፡
በዓሉ በዋና ከተማዋ ሞስኮ ቀዩ አደባባይ በተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ወታደሮቻችን ለመላው አውሮፓውያን ነጻነትና ክብር ውድ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ብለዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ የቀድሞ ወታደሮችና የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት መታደማቸውን ሩሲያ ቱደይ ዘግቧል፡፡