Fana: At a Speed of Life!

ህጻናትና ወጣቶችን ከማህበራዊ ትስስር ገጾች ጎጂ ተጽዕኖ ለመታደግ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ኅብረት ህጻናትና ወጣቶችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ከሚደርስባቸው ጉዳት ለመታደግ የሚያስችል ጥብቅ ህግ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው፡፡

የኅብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን እንደገለጹት፥ ኅብረቱ በቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር) ላይ ርምጃዎችን ለመውሰድ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

በርካታ የማህበራዊ ትስስር ዘዴዎች ወጣቶች ብዙ ጊዜያቸውን መተግበሪያዎቹን በመጠቀም እንዲያሳልፉ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ስልቶችን ይጠቀማሉ ሲሉ ነቅፈዋል፡፡

በተለይም ቲክቶክ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያለገደብ ክፍት ማድረጉ ወጣቶችን ለማህበራዊ ትስስር ገጽ ሱስ የሚያጋልጥ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም የፌስቡክ እና ኢንስታግራም መተግበሪያዎች ከ13 ዓመት በታች ያሉ አዳጊዎች የማህበራዊ ትስስር ዘዴዎችን እንዳይጠቀሙ የሚከለክለው ህግ ተግባራዊ አለመደረጉን አንስተዋል፡፡

ማህበራዊ ትስስር ገጾች በአዳጊዎችና ወጣቶች ላይ እያስከተሉ ያሉትን ጉዳት ለመከላከል ጠበቅ ያለ ርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡

ኅብረቱ በዚህ ዓመት መጨረሻ የማህበራዊ ትስስር ገጾቹ የዕድሜ ገደብ እንዲያስቀምጡ አስገዳጅ መመሪያ ይፋ እንደሚያደርግ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.