Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከጃፓንና ደቡብ ኮሪያ መሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በሚቀጥለው ሳምንት ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ እና ከደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ጋር ሊወያዩ ነው።

መሪዎቹ የሚያካሂዱት የሶስትዮሽ ውይይይት በፈረንጆቹ  የፊታችን ታህሳስ 24 ቀን በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቸንግዱ ከተማ የሚያካሄድ መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከሶስትዮሽ ውይይቱ በፊትም ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሀገራቱ መሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የተናጠል ውይይት የሚያድርጉ መሆኑ ተመላክቷል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፥መሪዎቹ በሶስትዮሽ ውይይታቸው  በተለያዩ ቀጠናዊና እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ መሆኑን አስታውቋል

በተለይም በሰሜን ኮሪየ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ዙሪያ በጥልቀት የሚመክሩ መሆኑ ነው የተገለጸው።

በቅርቡ ሩሲያ እና ቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰሜን ኮሪያ ላይ ከጣላቸው ማዕቀቦች ውስጥ የተወሰኑት እንዲነሱ ሃሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ይህም ሰሜን ኮሪያ በኒውክሌር የጦር መሳሪያ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር የምታደርገውን ድርድር እንደ አዲስ በመጀመር አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያበረታታ መሆኑ ተገልጿል።

አሜሪካ በበኩሏ በሩሲያ እና ቻይና የቀረበው ረቂቅ ሃሳብ በትክክለኛው ጊዜ ያልቀረበ ከመሆኑ ባሻር የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ስትል አጣጥላዋለች።

ምንጭ፦  ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.