ሀገራዊ ምክክሩ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ተቀራርበው ለመፍትሔ እንዲነጋገሩ እድል ሰጥቷል – ምሁራን
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በያገባኛል ስሜት ተቀራርበው ለመፍትሔ እንዲነጋገሩ እድል ሰጥቷል አሉ ምሁራን፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በህዝቦችና በልሂቃን መካከል የሰንበቱና የተራራቁ ሀሳቦችን በማስታረቅ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል፡፡
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር መምህር ሰለሞን ኪዳኔ፤ ሀገራዊ ምክክር ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በያገባኛል ስሜት ተቀራርበው ለመፍትሔ እንዲነጋገሩ እድል የሰጠ ነው ብለዋል።
ባለፉት መንግሥታት የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሁሉን አካታች አለመሆኑ ሀገርን ለተለያዩ ችግሮች መዳረጉን አንስተዋል።
በተጨማሪም ምክክሩ በእስካሁን ሂደት አሳታፊ እና ለገዢ ሀሳብ ቦታ የተሰጠበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዋቅጅራ አለሙ በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ምክክሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማሳተፉ ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
በምክክሩ ሁሉም ሀሳብ መስተናገዱ ለሀገራዊ ሰለም እና መረጋጋት ሁነኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አብራርተዋል።
ምሁራኑ ባለፉት ዓመታት ለሀገራዊ አንድነት እና መግባባት ምክክሩ የሀሳብ ሜዳ ሆኖ መፍትሔ ለማበጀት የሄደበት ርቀት አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።
ለምክክር ሂደቱ መሳካት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ቁልፍ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
በወርቅአፈራው ያለው