ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በመዲናዋ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል።
የምረጡኝ ቅስቀሳው በከተማዋ ስድስት ኪሎ ሰማዕታት አደባባይ፣ አራት ኪሎ አርበኞች አደባባይ እንዲሁም መገናኛ እና ቦሌ አካባቢዎች የቅንጅቱ አመራሮችና አባላት በተገኙበት ነው የተካሄደው፡፡
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ተግባር ላይ ውለው ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍትሔ ያመጣሉ ያላቸውን አማራጮች እያስተዋወቀ ይገኛል።
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ መኢአድና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ በጥምረት የመሰረቱት ቅንጅት ሲሆን፥ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱ አውራ ጣት መሆኑ ይታወቃል።
በግዛቸው ግርማዬ