Fana: At a Speed of Life!

በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል፣ ለመመዝገብና ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መደበኛ የአሰራር ሥርዓት ሰነድ በዛሬው ዕለት አፅድቋል።
በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ሰነድ ጥቃቱ ሲከሰት ፈጣን ምላሽ ለመስጠትና የባለድርሻ አካላትን ኃላፊነት በግልጽ ለመለየት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በመድረኩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ጨምሮ 10 ተቋማት ኃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት ለመወጣት የማረጋገጫ ፊርማቸውን አኑረዋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ሰነዱ በምርጫ ወቅት የሴቶችን ደኅንነት፣ ክብር፣ እኩልነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ የተዘጋጀ ትልቅ የቁርጠኝነት ማሳያ ነው።
የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሻሻል ፆታዊ ጥቃቶችን በግልጽ መከላከልና ተገቢውን ምላሽ መስጠት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው÷ ፈራሚ ተቋማት በቅንጅትና በተጠያቂነት ስሜት መስራት እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን የቦርዱ መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.