Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካና እስራኤል የሚደረግ ጥቃት ጦርነቱ እንዲስፋፋ ያደርጋል ስትል ኢራን አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በአሜሪካ እና በእስራኤል የሚደረግ ምንም አይነት አዲስ ጥቃት ጦርነቱን ከቀጣናው ውጭ እንዲስፋፋ ያደርገዋል ሲል አስጠነቀቀ።
አሜሪካ እና እስራኤል ተደጋጋሚ ካጋጠማቸው ስትራቴጂካዊ ሽንፈት መማር ተስኗቸዋል ብሏል።
የሁለቱ ሀገራት የጦር ኃይሎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ጥቃት ቢሰነዝሩም፤ ኢራን እስካሁን ድረስ ሁሉንም አቅሟን ላይ እንዳልተጠቀመች ገልጿል።
በኢራን ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ከተደጋገመ ጦርነቱ ከቀጣናው አልፎ በአካባቢው ይስፋፋል ሲል ማስጠንቀቁን ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።
ምንም ዓይነት ጥቃት ቢሰነዘር ባልተለመደ እና ባልተጠበቀ መልኩ ምላሽ እንደሚሰጥም የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አስታውቋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት ቀናት በፊት በኢራን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በባህረ ሰላጤው መሪዎች ጥያቄ መሰረት ለሌላ ጊዜ ተላልፏል ማለታቸው ይታወሳል።
ፓኪስታን በፈረንጆቹ ሚያዚያ 8 የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የተቋረጠውን ዲፕሎማሲ ለማደስ እየሰራሁ ነው ብላለች።
በአቤል ነዋይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.