Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን በዛሬው ዕለት መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዟችን አካልና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እመርታ ትልቅ ማሳያ የሆነው የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል ብለዋል።
ቁልፍ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን መሰል ፋብሪካዎች ግንባታ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ በመላ ሀገሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
‎ፋብሪካው የዓለም ዓቀፍ ጥራትና ተወዳዳሪነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን እንደሚያቀርብ ገልጸው ÷ ለምርቱ የሚያስፈልጉትን ጥሬ ዕቃዎች ከ80 በመቶ በላይ ከሀገር ውስጥ ዐቅም እንደሚያገኝ ጠቁመዋል።
ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብትና እምቅ ጸጋ የመጠቀም ብቃቷን ከመገንባቱ ባሻገር ከውጭ ገቢ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስም አውስተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.