Fana: At a Speed of Life!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የተመረቀው ግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ምን አይነት ሴራሚኮችን ያመርታል፡-

👉 ‎ፋብሪካው የተገነባው በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ነው፣
👉 መሰረት ልማቱ በ300 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን÷ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ የሴራሚክና የፖርሲሌን ንጣፎችን ያመርታል፣
👉 ፋብሪካውን ከዕቅድ ጀምሮ እስከ መሬት ዝግጅት ብሎም ሙሉ ሥራ ማስጀመር የወሰደው ጊዜ ዘጠኝ ወራት ብቻ ነው፣
👉 በአሁኑ ወቅት 60×60 የሴራሚክ ንጣፎችን በስፋት ማምረት ጀምሯል፣
👉 በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የምርት ዓይነቶቹን በማስፋት የ80×80፣ 60×120፣ 70×140 እና 80×160 መጠን ያላቸውን የንጣፍ ዓይነቶች እንዲሁም የአውሮፓን የጥራት ደረጃ ያሟሉ የፖርሲሌን ምርቶችን ማቅረብ እንደሚጀምር ይጠበቃል፣
👉 ፋብሪካው ከ2 ቢሊየን ብር በላይ መዋዕለ ነዋይ የወጣበት ሲሆን÷ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ያመላከተ ክንውን ነው፣
👉 ለፋብሪካው ምርት የሚያስፈልጉት ጥሬ ዕቃዎች 80 በመቶ የሚሆነው ከፋብሪካው በ100 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ይገኛል፣
👉 የፋብሪካው መከፈት የውጭ ምርት ጥገኝነትን የሚቀንስ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችላትም ጭምር ነው፣
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.