Fana: At a Speed of Life!

ሁዋዌ በአፍሪካ ምርጥ አሰሪ ተቋም በመሆን በድጋሚ እውቅና አገኘ

ሁዋዌ በተያዘው የፈረንጆቹ 2026 በጀት ዓመት በአፍሪካ ምርጥ አሰሪ ተቋም በመባል እውቅና አግኝቷል፡፡

ቶፕ ኢምፕሎየርስ ኢንስቲትዩት የተሰኘው ተቋም በአፍሪካ በተለያዩ መስፈርቶች ምርጥ አሰሪ የሆኑ ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረትም ሁዋዌ ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ከፍተኛ የሥራ እድል ፈጣሪ ምጥ አሰሪ ተቋም በመሆን እውቅና ማግኘተ ችሏል፡፡

ኩባያንያው በሞሮኮ፣ግብጽ፣ካሜሮን፣ማሊ፣ አልጄሪያ እና ኢትዮጵያን ጨም በ10 አፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ የሥራ እድል ፈጣሪ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ቶፕ ኢምፕሎየርስ ኢንስቲትዩት የዓመቱ በሥራ እድል ፈጠራ፣ በሰው ሃብት አስተዳደር፣ ደህንነቱ በተጠበቀ የሥራ ከባቢ እና የሰራተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተቋማትን በመለየት እውቅና ይሰጣል፡፡

መስፈርቶቹ በስድስት ዋና ዋና የሰው ሃብት አስተዳደር ዘርፎች ላይ የተመሰረቱ ሲሆን÷ እነዚህም የአመራር፣ የክህሎት፣ ሥራ ፈጠራ፣ሥልጠና፣ ብዝኃነትና አካታችነት እንዲሁም የሥራ ቦታ ደህንነት ናቸው፡፡

ሁዋዌ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረወን ጥረት ለማገዝ እና የጋራ እሴት ለመፍጠር ከሀገሪቱ መንግሥት፣ ከኢንተርፕራይዞች እና ሀገር በቀል አጋሮች ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.