Fana: At a Speed of Life!

በወታደራዊ ሥነ ምግባር የታነጸ ገለልተኛ ሠራዊት እየተገነባ ነው – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በአስተሳሰብና አደረጃጀት ገለልተኛ የሆነ ሠራዊት እየተገነባ ነው አሉ።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ዕጩ መኮንኖች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በዚህ ወቅት ፥ ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ያለው ሚና በፖሊስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑንና የዛሬው ምረቃ የሪፎርም ትግበራው ወጤት መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋሙ አሁን ባለው ጠንካራ የመፈፀም አቅም በኢንተርፖልና በመሠል ዓለም አቀፍ የፖሊስ ተቋማት ንቁ ተሳትፎ መሪ ተዋናይ መሆን ችሏል ነው ያሉት፡፡

ተቋሙ በሰለጠነ የሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ እና በዘመናዊ ትጥቅ የተደራጀ በመሆኑ ባንዳ እና ባዳ የሚሸርቡትን ሴራ በአጭር ጊዜ በማምከን ሕልማቸውን ባዶ ማድረግ መቻሉን አውስተዋል፡፡

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.