Fana: At a Speed of Life!

ሻምፒዮኑ አርሰናል ዋንጫውን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው አርሰናል በዛሬው ዕለት ዋንጫውን ተረክቧል፡፡

ባለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አርሰናል÷ በዚህ ዓመት አንድ ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮን መሆኑን ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ የሊጉን የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በማድረግ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በጨዋታው የአርሰናልን ግቦች ጄሱስ እና ማዱኬ ሲያስቆጥሩ ማቴታ የክሪስታል ፓላስን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የቡድን ግንባታ ሒደት ከ22 ዓመታት በኋላ ከሊጉ ዋንጫ ጋር የተገናኙት መድፈኞቹ ዛሬ ምሽት በሴልኸረስት ፓርክ ነው ዋንጫውን በክብር የተቀበሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.