Fana: At a Speed of Life!

ለህዝባችን የገባነውን ቃል ለመፈፀም የማያቋርጥ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለህዝባችን የገባነውን ቃል ለመፈፀም የማያቋርጥ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
7ኛው የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አግልግሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።
የማዕከሉን ለአገልግሎት መብቃት አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ አዲስ ባለ 6 ወለል ህንፃ ገንብተን በቴክኖሎጂ አደራጅተን ለአገልግሎት ክፍት በማድረጋችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ለዘመናት በተንዛዛ አሰራር እጅ መንሻ እየተጠየቀ ዜጎችን ሲያማርር የነበረውን የመንግሥት አግልግሎት አሰጣጥ ችግር ስርነቀል በሆነ መልኩ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በመፍጠንና መፍጠር መርህ፤ የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ የዘመነና ፍትሃዊ ለማድረግ አንድ ተብሎ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አግልግሎት 7ኛው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ማዕከል ለአግልግሎት ክፍት መደረጉን ገልጸዋል።
የማዕከላቱ መበራከት አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ህዝብ ወደ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች በመሄድ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ በተንቀሳቃሽ የአዲስ መሶብ አገልግሎት ይበልጥ ወደ ህዝቡ እንዲጠጋ በማድረግም ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል ብለዋል።
ለህዝባችን የገባነውን ቃል ለመፈፀም እንዲሁም የምናልመውን ብልጽግና እውን እንዲሆን ተከታታይነት ያለው የማያቋርጥ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን ነው ያሉት።
ኑ በሚቀርባችሁ ማዕከል ያለምንም መንገላታት በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቀሙ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.