Fana: At a Speed of Life!

የቀጣናው ኃይሎች ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮች ጋሻ ሊሆኑ አይችሉም – ኢራን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የቀጣናው ኃይሎች ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮችን ከቴህራን አጸፋ ሊከላከሉ አይችሉም አሉ።
የአሜሪካ ኃይሎች፣ የጦር ሰፈሮች እና በመካከለኛው ምስራቅ ያላት ፍላጎቶች ከአሁን በኋላ ከጥቃት እንደማይድኑ አስጠንቅቀዋል።
በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ለሦስት ወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም ድርድር በሚደረግበት ወቅት ነው የኢራን መንፈሳዊ መሪው ይህንን መግለጫ ያወጡት።
መሪው ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ከሰጡት ጠንካራ መግለጫዎች መካከል ይህ አንዱ ነው መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል።
አሜሪካ በደቡባዊ ኢራን በሚገኙ የኢራን የሚሳኤል ቤዞች እና ፈንጅ ሲቀብሩ ነበር ባለቻቸው ጀልባዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈፅማለች፡፡
የአሜሪካ የአየር ጥቃት እና የሞጅታባ ኻሜኒ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተካሄደ የሚገኘውን ድርድር ተፅዕኖ ውስጥ ሊከተው ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
በብርሃኑ አበራ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.